Shobole Engineering

የሊፍት ጥገና እና አገልግሎቶች በኢትዮጵያ


   አሳንሰሮች በኢትዮጵያ የህንፃ ግንባታ ውስጥ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። እነዚህ የህንፃ ላይ የመጓጓዣ ዘዴዎች ረዣዥም ሕንፃዎች ላይ ለመጓጓዣነት ያገለግላሉ፡፡ይህም በከተማ ውስጥ ያለውን የህንፃ ግንባታ መስፋፋትን ያግዛል፡፡በመሆኑም በአንድ ህንፃ ላይ ሊፍት መኖሩ የህንፃውን ጥራት ይጨምራል ፡፡ በተጨማሪም የንግድ ድርጅቶችን እና ነዋሪዎችን ወደ ከተማ ማዕከሎች እንዲሳቡ ያደርጋል ፡፡ ከዚህም በላይ አሳንሰሮች በህንፃዎች ውስጥ የመጓጓዣ ቅልጥፍናን በማሻሻል ምርታማነትን ይጨምራሉ በተጨማሪም አሳንሰር የመሬት አጠቃቀምን በማመቻቸት እና አግድም የማስፋፊያ ፍላጎትን በመቀነስ ለዘላቂ የከተማ ልማት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

   የህንፃዎች አሳንሰር ኢትዮጵያ የከተማ ቦታዎቿን እምቅ አቅም እንድትጠቀም በማድረግ ታላቅ ሚና ይጫወታሉ ፤የአሳንሰሮች መደበኛ ፍተሻና ጥገና  ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማ አገልግሎት ለማግኘት ያግዛል ።ሊፍት ብልሽቶችን ለመከላከል ፣የተሳፋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና እድሜያቸውን ለማራዘም መደበኛ ጥገና ማካሄድ በጣም ጠቃሚ  ነው፡፡

የአሳንሰር ጥገና አስፈላጊነት

    አሳንሰሮች ተሳፋሪዎችን እና እቃዎችን በተለያዩ ፎቆች መካከል የማጓጓዝ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህም በኪነ-ህንፃ ስራ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ያደርገዋል። በአሳንሰር ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ከማጋጠማቸው በፊት መለየት እና መፈታት አለባቸው ይህም ሊፍቱ አስተማማኝ እና ለተጠቃሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑንማረጋገጥ ያግዛል።

   የአሳንሰር ድንገተኛ ብልሽት ወደ ከፍተኛ ችግር ሊያመራ ይችላል ይህም የአካል ጉዳት ወይም የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ፡፡ አሳንሰሮች በእለት ተእለት የግንባታ ስራዎች ላይ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ በመሆኑም ለአሳንሰሮች ጊዜውን የጠበቀ ጥገና አለማከናወን የስራ ጊዜያቸው እንዲያጥር እና  ተሳፋሪዎች እና ጎብኚዎች ላይ ከፍተኛ ችግር እንዲፈጥር ያደርጋል፡፡ በጣም በከፋ ሁኔታ ውስጥ፣ የተራዘመ የአሳንሰር መቆራረጥ የንግድ ስራዎችን ሊያስተጓጉል ይችላል፣ ይህም ለኪሳራ እና ለህንፃው አስተዳደር መልካም ስም መጥፋት ያስከትላል።

የአሳንሰር ጥገና መመዘኛዎች

የአሳንሰር ጥገና በተለያዩ ምክንያቶች ሊለያይ ይችላሉ፣የሊፍት አይነት፣ እድሜው፣ ውስብስብነት እናአገልግሎት አሰጣጡን  ጨምሮ።

የአሳንሰር አይነት፡- እንደ ሃይድሮሊክ፣ ትራክሽን፣ ወይም ፓሴንጀር ሊፍት ያሉ የተለያዩ አይነት ሊፍቶች የተለያየ የጥገና መስፈርቶች አሏቸው። እያንዳንዱ አይነት የተወሰኑ የጥገና  ክፍሎች እና ዘዴዎች ሊኖራቸው  ይችላል፡፡

ዕድሜ እና ሁኔታ፡ የቆዩ አሳንሰሮች በብቃት እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲሰሩ ለማድረግ ብዙ ተደጋጋሚ እና ሰፊ ጥገና ሊያስፈልጋቸው ይችላል።

የአገልግሎት ደረጃ፡ የአሳንሰር ጥገና ደረጃዎች ከመሠረታዊ የመከላከያ ጥገና እስከ አጠቃላይ የጥገና እና የአደጋ ጊዜ ጥሪዎችን የሚሸፍኑ ፓኬጆችን ጨምሮ በተለያዩ የጥገና ደረጃዎች አላቸው፡፡

የጥገና ድግግሞሽ፡ ከፍተኛ ትራፊክ እና የምልልስ ጫና  ባለባቸው ሕንፃዎች ውስጥ የሚገኙ አሳንሰሮች ብዙ ጊዜ ፍተሻ እና ጥገና ሊያስፈልጋቸው ይችላል።

ቴክኒሻኖች- የአሳንሰር ጥገና በተመሰከረላቸው አስፈላጊው እውቀትና ስልጠና  ባላቸው ቴክኒሻኖች መከናወን አለበት። የተመሰከረላቸው ባለሙያዎችን መቅጠር አሳንሰሮቹ ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ ያግዛል፡፡

  የሊፍት ጥገና አገልግሎት በኢትዮጵያ

 በኢትዮጵያ ሾቦሌ ኢንጂነሪንግ እና ሌሎች ጥቂት የአሳንሰር ኩባንያዎች በአሳንሰር እና በእስካሌተሮች ማምረት እና ጥገና አገልግሎት ላይ  ተሰማርተው አስተማማኝ አገልግሎቶች እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

 ሸቦሌ ኢንጅነሪንግ በድርጅቱ ለተመረቱ እና ለተጫኑ ሊፍቶች የዋስትና ጊዜ ውስጥ ሙሉቴክኒካል እገዛና ከሽያጭ በኋላ ተገቢውን የጥገና አገልግሎቶችን በተጨማሪም  ለሌሎች የሊፍት ብራንዶች የተሟላ ጥገና አገልግሎት ይሰጣል።

Destek Hattı